Friday, January 12, 2024

ግመልሽን አጠጪበት

 



የባህር በር

ፈረሴን ቀይባህር ነው የማጠጣው፡ የሚሉ ነገስታት ሀገር የነበረችው ኢትዮጲያ፤ ከማያባራ ረጂም ጦርነት በሁዋላ ለሁለት ስትከፈል ረጂሙን የባህር በር ለትንሽዋ ኤርትራ፡ ግመልሽን አጠጪበት ብላ ሰጥታት፡ መተንፈሻ በሩዋን ከቆለፈችበት ሶስት አስርት ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል፡፡ ከቀይባር መታጣት በሁዋ ከራሷ ተነጥላ አገር፤ የሆነችውን የሚጢጢዋን ጂቡቲን የመተንፈሻ በር ፡ በኪራይ በመጠቀም ለመተንፈስ እየሞከረች ቢሆንም፡ የህዝብ ብዛት የፈጠረው ከፍተኛ ፍላጎት፡ አለምን እያናወጠ ከመጣው የኑሮ ውድነት ጋር ተዳምሮ፡ የጂቡቲው መተንፈሻ በር በቂ አለመሆኑን ከባድ ማስጠንቀቂያ እየሰጠ ባለበት ሰአት፤ ኢትዮጲያ ከኤርትራ ጋር ሰላም መፍጠሩዋ ሁለቱን ሀገራት በአየርና በመሬት የሚያገናኛቸው መንገዶች፡ ስራ እንዲጀምር በሁለቱም መሪዎች በኩል ያለው ቁርጠኝነትና ቶሎ ወደስራ መገባቱም፡ ለእኛ ለኢትዮጲያዊያን ትልቅ ተስፋ ነበር፡፡ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ያ ተስፈ ቀስ በቀስ እየሟሸሸ፤ ከሄደ ዋል አደር ከማለቱም በላይ ሌላ ባህር በር መፈለግ እንደሚገባን፡ ከመንግስት በኩል፤በይፋ ለእኛም ለዓለሙም አንዴ ተነገረን፡፡ ይህ ሲነገር በአስፈላጊነቱ ላይ ማንም ኢትዮጲዊ ግን ጥያቄ ይኖረዋል ብዬ አላስብም ነበር፡፡ ግን ከማን በኤርትራ በኩል፡ ወይስ በጂቢቱ የሚሉት ጥያቄዎች ውስጤ እየተብላ ነበር፡፡ ይህ ሃሳብ በተነሳ ሰሞኑን በርካታ ሚዲያዎች፤ ምሁራን፤ፓለቲከኞች፡ የእኔ ብጤ ተራ ዜጎችም፡ ሀሳቡን በሰፊው ሲወያዩበት ነበር፡፡ ከበርካታ ጊዜያት በሁዋላ ሁላችንም በሀገር ጉዳይ አብረን እንድናስብ ያደረገ ሃሳብ ስለነበር ተወዳጅ ነበር፡፡

አሁንም ከዕለታት በአንድ ቀን በፈረንጆቹ አዲስ አመት የመጀመሪያ ቀን በወርሃ ታህሳስ ኢትዮጲያና ሶማሊላድ በወደብ ጉዳይ መፈራረማቸውን በማህበራዊ ገጽ አየሁት፡ ትንሽ ስራ ላይ ስለነበርኩ ፡ዘርዘር ያለውን መረጃ አላየሁትም፡ ነበር፡፡ ከተወሰኑ ሰዓታት በሁዋላ በርካታ ገጾች ሰበር ዜና በሚል በርካታ ነገር ጽፈው አነበብኩ፡፡ ውስጤ ደስ፤ሲለው ብቻዬን መሳቄን አስታውሳለሁ፡፡ የሚመሰገነውን እያመሰግንኩ፤ በጉዳዩ ላይ ከማንም ሳላወራ ከስራ፡ወደ ቤቴ እየገባሁ፡ ዜናዎቹን በጥንቃቁ እንደገና ማንበብ ጀመርኩ፡፡ የውሸት ዜና እንዳይሆን በመመኘት፡፡ ተረጋግቼ ሳነበው ሶማሌያ ብዬ ያነበብከት ለካ ሶማሌላንድ ነው የሚለው፡ ውስጤ ግራ ተጋባ በወቅቱ፡ ጭንቅላቴ የመጣው ቻይናና ታይዋን ናቸው፡፡ ሀገር ነኝ አይደለሽም የሚለው እሰጥ አገባ፡ የሚያደርጉትን፡በማሰብ፡ ስለሶማሌላንድ እና ሶማሊያ ደግሞ በቅርብ አመታት ውስጥ ያለውን ጉዳይ ጥርት ያለ መረጃ አልነበረኝም፡፡ ሶማሌላንድ ግን ሀገር እንዳልሆነች አውቃለሁ፡፡ መንገድ ላይ እያለሁ፡ በርካታ መኪናዎች እንኳን ደስ አላችሁ የዘመናት ጥያቄ በሰላም ተፈታ እያሉ በድምጽ ማጉያ የሰላም መልዕክት ሲያስተላልፉ፡ እየተገረምኩኝ ነበር፡፡

ቀስ እያልኩ መረጃዎችን ሳጣራ፡ የሶማሊያ መንግስት ነገ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያደርግ፡ ከስብሰባው በሁዋላ መግለጫውን ፕሪዚዳንቱም ማደሪያቸውን ለኢትዮጲያ ጠላቶችና ከጎኔ ይቆማሉ ላሉዋቸው ሁሉ ስልክ ሲደውሉ ደብዳቤ ሲጽፉ አደሩ ከረሙ፡፡ ኢትዮጲያን ለማቃጠል ደረቅ ሳር ባገኘሁ ክብሪቱ እኔ ዘንድ አለ፤ በማለት ሁሌም ዝግጁ የሆነችው ግብጽ፤ ጠላትሽ ጠላቴ አለሁ አለች፡፡ ይችን እኛም ስለምናውቅ ብዙ አልገረመንም፡፡ ይልቅስ ጉዳዩን ወደ ጸጥታው ምክርቤት፡ ከህዳሴ ግድብ ጋር አያይዘን እናቅርበው አለሟላቷ ብቻ ነው፡ እኔን የገረመኝ፡፡ በርግጥ ከቀናት በሁዋላ ይህንን ምክር እንደምትመክራት አልጠራጠርም፡፡ እንዴው በኢትዮጲያና በሶማሌላድ መካከል የተደረገው የፊርማ ስነስርዓት ከተከናወነበት ሰዓት አንስቶ ማን ምን አለ የሚለው ስናይ

እንኳን የኢትዮጵያ ስብራት ጥገና ቀን በጋራ አደረሰን፤ አደረሳችሁ።በተደጋጋሚ ለህዝባችን ቃል በገባነው መሰረት ኢትዮጵያ ካሏት ዋና ዋና ስብራቶች መካከል አንዱ የሆነው ቀይ ባህርን #access የማድረግ በዛውም #የማልማት ፍላጎት ከሶማሌላንድ ወንድሞቻችን ጋር በተደረገው የትብብር ስምምነት ዛሬ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመናል። ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንዳነሳነው እኛ ያሉንን ሃብቶች የመጋራት ፣ የመካፈልና በጋራ የመልማት ፍላጎት እንጂ ማንንም በኃይል የማስገደድ ፍላጎት የለንም ስንል የነበረው ሃሳብ በተግባር ዛሬ በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያው ቀን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ የሶማሌላንድ ህዝብና ለሰላም ወዳድ ህዝብ ለልማት ወዳድ ህዝብ የምናበስረው የምስራች ይሆናል። ስብራቶቻችን ይጠገናሉ፣ ኢትዮጵያ ትበለፅጋለች። በገባነው ቃል መሰረት ሀገራችንን ወደሚቀጥለው ደረጃ እናሸጋግራለን። ስለሆነው ሁሉ ያደረገልንን ፈጣሪን እናመሰግናለን።”

ጠሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

" ለሶማሌላንድ ነፃ ሀገርነት እውቅና የምትሰጥ የመጀመሪያዋ ሀገር እንደምትሆን " በምላሹ ደግሞ ሶማሌላንድ ፤ ኢትዮጵያ የባህር በር እና የባህር ኃይል ቤዝ እንዲኖራት በቀይ ባህር በኩል 20 ኪሎ ሜትር የሆነ መሬት ለኢትዮጵያ በሊዝ እንደምትሰጥ ሲናገሩ ተደምጠዋል።”

የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ

 

የሱማሌ መንግሥት ስምምነቱን አውግዞታል

ኢጋድ በዋና ጸሐፊው በኩል«እህትማማች» ያሏቸዉ ሁለቱ አገራት፤ ሁኔታውን በሰላማዊ መንገድ ለማርገብ እንዲጥሩ መክረዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያና ሶማሊያ በመከባበር ላይ ተመስርተው  ውጥረቱን እንዲያረግቡት አሳሰበ

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር

በኢትዮጵያና በሶማሌላንድ መካከል የተደረሰውን የባህር በር የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተከትሎ፣በአፍሪቃ ቀንድ የሰፈነው ውጥረት አሳስቦኛል ስትል ዩናይትድስቴትስ አስታወቀች።ዩናይትድስቴትስ፣ ለሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ  የግዛት አንድነት ዕውቅና እንደምትሰጥም ገልጻለች።

የአሜሪካ አቋም

ራስ ገዟ ሶማሌላንድ "የሁለትዮሽ ስምምነት ለማድረግ " የሶማሊያ ፍቃድ አያስፈልገኝም ፤ አልጠይቅምም " ።  

 

እንደዚህ እየተባለ ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ መረሳት ያለበትና ሁላችንንም አንድ የሚያደርገን ጉዳይ የባህር በር ያስፈልገናል፡፡ ለመዋጋት ወይንም ሌላ ሀገር ለመቀራመት ሳይሆን ለመኖር፡፡ ቀይባህርን በምንም የማይጎራበቱ ሀገራት አለምን ለማፈራራት የጦር ቤዝ ሲገነቡበት እኛ ለመኖር ለወደብ እንጠቀመው ብለን መጠየቃችን ከፍትህም በላይ ፍትሃዊ ነው፡፡

 

No comments:

Post a Comment

                             ገበር አምባ                    ስራ ፈቶ ሲያሽ ያንች ተመልካች                       በውበት ቁንጅና ማን ነበር እንዳንች፡፡          ...