Thursday, June 26, 2025

ኢትዮጲያዊነት

                                                   ኢትዮጲያዊነት ማህበራዊ ገጾች

ከልጅነቴ እድገቴ እነዲሁም በእያንዳንዱዋ የክፍል ደረጃ ስለኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነት የሰማሁት፤ተማርኩት፤ ያነበብኩት፡ ሁሉም በግልም ሆነ በአንድ ላይ ሲታዩ እኛ ኢትዮጲያዊያን ደጎች፤ጀግኖች፤ሰው ወዳዶች፤ ሃይማኖተኖች፤ ፍትሀዊዎች ነን የሚል ነው፡፡ ለበርካታ አመታትም ይህንን መሰል መገለጫ በበርካታ ወገኖች ላይ አይቻሉ፤ ይህንን መልካምነታቸውን ያጋሩኝ በርካታ ወንድሞችና እህቶች ጓደኞች አፍርቻለሁ፡፡ እድሜ ላሳደገችኝ ቤተክርስቲያን ይሁንና የእነዚህ መልካም ሰዎች አበርክቶ ለህይወቴ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጎልኛል፡፡ በየደረጃው ያስተምሩኝ የነበሩ መ/ራኖቼ ይህንን መጽሐፍ ብታነበው፤ ያዋሱኝ ይህንን ብትመለከተው ብለው፤የተለያዩ ግለሰቦችን ታሪክ የሚያጋሩኝ ሁሉ፤ ውለታቸውን አልረሳም፡፡

ነገር ግን አሁን አሁን፤በማህበራዊ ሚዲያ የማነባቸው የምሰማቸው፤ የሚመለከታቸው ታሪኮችና ድርጊቶች ግን፤ከዚህ በጣም የራቁ ናቸው፡፡ አባት ልጁን ደፈረ፤ ልጅ አባቱን ገደለ፤ እናት ልጆቿን ጥላ ጠፋች፤ካህኑ ሴት ደፈረ፤ መነኮሳት በጥይት ተደብድበው ተገደሉ፤ የመሳሰሉት፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ሰዎች ፈተና በዝቶባቸው፤  ሊፈጽሟቸው፤ ለፈጸሙትም በደልና ክፍት ተገቢውና ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ቅጣት ሊጠብቃቸው ይችላል፡፡ እነዚህን ዜናዎችን የሚለጠፉ ልጥፎችን ተከትሎ ግን የሚሰጡ አስተያቶች እጅግ ልብን ያቆስላሉ፡፡ ይህንን የፈጸመው የዚህ ብሔር ተከታይ ስለሆነው፡ የእርሱን ወይንም የእርሷን ብሔር ተከትሎ ሌላ ጦርነት፤ ይህንን የፈጸመው የዚህ ሃይማኖት ተከታይ ስለሆነ ነው፤ የዚህ ፖለቲካ ድርጅት አባል ስለሆነ ነው፤ በማለት የጅምላ ፍረጃ እና አሰጥ አገባው፡ ግን እጅግ በጣም የሚያበሳጭ ከመሆኑም በላይ፡ ያ በመልካም ውስጤ አስቀምቸው የነበረው ኢትዮያዊነት ውሸት ነበር እንዴ ብዬ ውስጤ እንዲደክም ያደርገዋል፡፡ ጉዳዩን አጅግ አሳሳቢ የሆነብኝ፤ እቀነሰ ይሄዳል፤ መልካምነታችን ይህንን ክፉነታችንን ያጸይመዋል፤ በሂደትም ያጠቁረዋል፡ የሚል ትልቅ ተስፋ ስለነበረኝ ነው፡፡ መርዘሙን ባሰብኩት ጊዜ ግን፡ ውስጤ እጅጉን ይደክማል፡፡ መች ይሆን ይህንን ኢትዮጲያዊ መልካምነት፡ ተመልሶ የማው፡ እላለሁ፡፡ ሃሳቤ በማንም ላይ እጄን ለመጠቆም ሳይሆን ችግሩ የጋራችን መሆኑን በማመን፤ ራሴም አስተዋጽ ስላለበት ንስሃ ጭምር ቢሆነኝ ብዬ ነው፡፡



                             ገበር አምባ                    ስራ ፈቶ ሲያሽ ያንች ተመልካች                       በውበት ቁንጅና ማን ነበር እንዳንች፡፡          ...