አ-ፈ-ወ-ር-ቅ-------- Part-3
ጥር 21 /2008
የመጀመሪያ አብሮነታቸውን በነሰብለ ቤት ያደረጉት ሰብለና አፈወርቅ በ 15ኛው ቀን በአፈወርቅ ጋባዥነት የደብረሊባኖስ ገዳምና ሊያሳያትና ከገዳሙም በረከት ተካፍለው ሊመጡ፤ ወደ ደብረሊባስ ገዳም አቀኑ፡፡ ሰብለ ወደገዳም ከ አፈወርቅ ጋር ስትሄድ ተደብቃ ሳይሆን በትክክል ለወላጆቿ ነግራ አስፈቅዳ እንድትመጣ ስላደረጋት ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም እሄዳለሁ ፈቃድ ብላ ስትጠይቅ ወላጆቿ በተለይም እናቷ ከልባቸው ተደሰቱ እንጂ ምንም አይነት የማመንታት ሁኔታ አላሳዩም፡፡ አሰይ ተመስገን አምላክ የልጄን ልብ ወደአንተማ ከተጠራህልኝ ምን ጣጣ አለብኝ፤ ተመስገን አምላኬ እያለሁ እጃቸውን ወደ ላይ ዘርግተው አምላካቸውን አመሰገኑ፡፡ ሰብልዬ መሄዱንስ ይሁን ግን ከማን ጋር ነው የምትሄጂው፤ ብለው ጠየቋት፤ እማዬ ባለፈው እቤታችን መጥቶ ያስተዋወቅሁሽ፤ መምህሬ ነው ያልኩሽ ስትላቸው ወይ ያ እንደስሙ ወርቅ የሆነ ትሁት ልጅ፤ ከእርሱ ጋር ከሆነ እንኳ ደብረሊባኖስ ዋልድባም ሂጅ አሏት፡፡ እማዬ ደግሞ ዋልዳባ ምንድነው አላቻቸው፤ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማችውን የቦታ ስም፡፡ ወይ ልጄ በሀገራችን ካሉት ትልቅ ቅዱስ ስፍራዎች አንዱ ነው፡፡ በርካታ የበቁ አባቶች ይገኙበታል ሲባል እሰማለሁ እንጂ እኔም አላውቀውም፤ ግን አምላኬ ቢረዳኝ አዛኝቱ ብትፈቅድ አይቼው የአባቶቼን በረከት አግኝቼ ብሞት ደስታዬ ወደር የለውም፡፡ ግዴ የለም አንች ልጄ ድረሽልኝና በራስሽ መኪና ነው ከገዳም፤ገዳም የምታዞሪኝ፡ አሏት፤ በደስታ ስሜት ውስጥ ሆነው፡፡ የሰብለ እናት ወ/ሮ ደጅ ይጥኑ አፈወርቅን በጣም አድርገውን ነው የወደዱት እርጋታው ጨዋታ አዋቂነቱ ትህትናው፤ በዚያም ላይ መልከ መልካነቱ ልባቸውን ስለማረከው፤ እንዴው አምላኬ አንተ ምን ይሳንሃል የማያልቅብህ ነህ፤ ለልጄ ውሃ አጣኝ ብታደርገው ብለው በምኞት ነጉደዋል፡፡ የአዋቂነቱን መጠንን ሲያጎላላቸው ስለቤተክርስቲን ብዙ ግድ የሌላት ልጃቸውን ወደገዳም ሊወስዳት አስቧል፡፡ እርሳቸውም ልባቸው በሀሴት ጮቤ ረገጠ፡፡ ሰብለና አፈወርቅ በተቀጣጡሩት አውቶቡስ ተራ በሰዓቱ ተገናኙና በሎንችን መኪና ወደገዳሙ አቀኑ፡፡ ዕለቱ ወርሃዊ የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓል ስለነበረ፤በርካታ የአዲስ አባባ ነዋሪዎች ነጭ ልብሳቸውንለብሰው ጧፍ እጣናቸውን አንግበው ወደ ገዳሙ ስሚሄዱ መኪና ከወትሮው በተለየ ወደ ገዳሙ ይበዛል፡፡ አፈወርቅና ሰብለ አዲስ አበባ ከተማን ወጣ እንዳሉ ሱልልታ፤ጫንጮ፤ ሙከጡሪ የመሳሰሉት የገጠር ከተሞች እያዩ አንዴ አንዱን እያነሱ ሲጥሉ ጉዞዋቸውን እያገባዱ ሳለ፡ ሰብለ ባለፈው ከአዲስ አበባ ውጭ የሄድሽባቸውን ቦታዎች ስትነግሪኝ እኮ በጣም የሳቅሁብኝ እርሱ እኮ እዚያው አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ፤ ቦታዎች ናቸው፡፡ ገጠሪቱ፤ኢትዮጲያን በፍጹም አታዊቂያትም፡፡ ሰውና እንሰሳ አብሮ እያደረ ፤የሰውልጅ ከእንጨትና ከኩራዝ ውጭ መብራት ሳይኖረው የሚኖርበት፤ እህሉን ከጎተራ ወተቱን ከእንስራ እያወጣ ከሚኖረው የከተማ ዋስትና የሆነውን ገጠሩን አላየሸውም፡፡ አይንሽ ከአድማስ አድማስ የተዘረጋ የእህል አዝመራ አላየም፡፡ ከብቶች በአረንጓዴ፤ለምለም መስክ ጠግበው ሲቦርቁ አላዚያም ተኝተው ሲንፈላሰሱ አላየሽም፡፡ ሴቶች በጀርባቸው እንስራ ተሸክመው ብዙ ኪሌሚትሮች ውሃ ቀድተው ሲመጡ፤ በጀርባቸው የገበያ ቁሶቻቸውን፤ገብይተው ሲመለሱ፤ መች አየሽውና፡፡ አንድ በቅርቡ የወጣ የአማሪኛ ዘፈን አለ በጣም ነው የምወደው፡፡ ምንም እንኳ ዘፈን ባላዳምጥም አንዳንድ ባህላዊ የሆኑ ዘፈኖች ግን ልቤን ይመስጡታል፡፡ ዘፋኙ ማን ነው እንዳትይኝ አደራ ከዘፈኑ ውስጥ አዝማቹ ግጥም ግን
ገና ገና ገና ምን አይተሸ
ልሂድ ትያለሽ
እያለ፤ ገጠሩን የጎጃም ምድር ብዙ እንዳለውና ምኑንም እንዳላያችው ከከተማ ለመጣች አንዲት ሴት ድራማዊ በሆነ መንገድ እያሳያት የሚዘፈን ዘፈን ነው፡፡ ከልቤ ነው የምወደው፡፡ ስለዚህ ሰብለ አዲስ አበባ ተወልደሽ አድገሽ ኢትዮጲያዊ ነኝ ማለት ከባድ ነው፡፡ አንድ እንጀራ በቢላ እየተቆረጠ ከሚቀርብብት ከተማ ሆነሽ፤ ወደ ገጠር ስትገቢ ለአንድ ሰው ሁለትና ሶስት እንጀራ ሲቀርብ፤ ቤት ካልገባችሁ ተብሎ መንገደኛ ከመንገድ ተጠርቶ ተጋብዞ የሚሄድበት ሀገር፤ ገጠር እያለ አዲስ አበባ የትልቋ ኢትዮጲያ ወካይ ሆና መቅረብ አትችልም፡፡ ስለዚህ ተማሪ ሰብለ ኢትዮጲያ የምትባለውን ሀገር በፍጹም አታውቂያትም በርግጥ ኢትዮጲያዊነትን በመወለድ አግኝተሸዋል፡፡ አሁን ደግሞ ከምትማሪው የትምህርት መስክ አንጻር ኢትየጲያን ማወቅ ግድ ይላል፡፡ ሰብለ የሃፍረት ስሜት እየተሰማት ቢሆንም ሳቅ እያለች ተስፋ አድርጋለሁ ወደፊት ሀገሬን አያታለሁ፡፡ እንግዴህ ዛሬ ከአዲስ አበባ ውጭ መጀመሬ አንድ ተብሎ ይቆጠረልኝ አለች፡፡ ኖ ማየት አለብሽ አልኩኝ እንጂ እስከአሁን ለምን አላየሸም ብዬ አልተቆጣሁም፤ ብሎ ዘና እንድትል አደረጋት፡፡ ለመሆኑ ስለደብረ ሊባኖስ ገዳም ምንታውቂያለሽ ብሎ ጠየቃት፡፡ አረ ምንም አላወቅም ግን በአንድ ወቅት አንተ ስታስተምር ገዳማት ትልቅ የኢትዮጲያ ቅርሶች ናቸው፡ ለቱሪዝምም የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፤ ስትል ከሰማሁት ውጭ አለችው፡፡ ደብረ ሊባኖእ ኢትዮጲያ ካሉዋት ጥንታዊ ታሪካዊ ገዳማት አንዱ ሲሆን በጻድቁ ኢትዮጲያዊ ተክለኃይማኖት ስም ጽላት ተቀርጾለት ቤተክርስቲያን ታንጾበት፤ ዘርፈ ብዙ የሆኑ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡ ግን የተክለሃይማኖት ገዳም ነው እንዴ ደብረ ሊባኖስ አይደለም እንዴ የሚባው አለች፤ ሰብለ፡፡ ልክነሽ የቦታው ስያሜ ከመካከለኛው ምስራቅ በተለይም ከሶርያም ከመጡ ቅዱሳኖች አንዱ በሆኑት አባ ሊባኖስ የተሰየመ ነው፡፡ አባ ሊባኖስ በቦታው ከአርባ አመት ላላነሰ ጊዜ ሲጋደሉ የነበረ ሲሆን አምላካችን ወደ እርሳቸው መጥቶ ከአንተ በኋላ የሚነሳ ታላቅ ቅዱስ አለ ይህ ቦታ የእርሱ ነው ለአንተ ያዘጋጀሁልህ ሌላ ቦታ አለ ብሎ አባሊባኖስ ወደ ሰሜን ኢትዮጲያ እንዲሄዱ ሲያደርጋቸው፤ ስሙ ግን በእርሳቸው እንዲጠራ ፈቃዱ ስለሆነ የጻድቁ ተክለሃይማኖት ገዳም ሆኖ በአባ ሊባኖስ እንዲጠራ ተደርጓል እንጂ ጽላቱ ግን የኢትዮጲያዊ ጻድቅ አቡነ ተክለሃይማት ነው አለና አዲስ የማታውቀው ታሪክ ነገራት፡፡
የኢስድሮስ ሆቴሎችና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማኔጅንግ ዳይሬክቴርና ባለቤት አቶ አጽናፍ ሰገድ ደብረሊባኖስ ገዳም ደርሰው መኪናቸውን ማቆሚያ ቦታ ሲፈልጉ ከህዝብ ሎንቺና ውስጥ ሁለት ወጣቶች ወርደው ሴቷ ጀርባውን ያዝ አድርጋው ለመሳለም ወደ ውስጥ ሲዘልቁ እየተመለከቱት ያለው ነገር ግራ አጋብቷቸዋል፡፡ እንዴ ይህ አፈወርቅ አይደለም እንዴ፤ ስሟን ባላውቃትም ይህች ልጅም የኮሌጃችን ተማሪ ናት እና በምን መልኩ ነው፤ አንድ መ/ሬና ተማሪዬ አንድ ላይ ሆነው ገዳም የመጡት፡፡ ዘመድናቸው እንዳልል አፈወርቅ በዝምድና በኮሌጃችን ያስመዘገበው ልጅ፤ እህትም ሆነ ወንድም የለውም፡፡ እና ምንድነው፡፡ አንድ በስነምግባር የታነሰ ትልቅ ሰው ነው ብዬ ተስፋ የጣልኩበት ሰው እንደዚህ ከራሴው ተማሪ ጋር ከወላጅ በአደራ ተቀብዬ፤ ከጉሮሮዋቸው እየነጠክሁ በየወሩ ክፍያ ተቀብዬ ከማስተምራቸው ተማሪዎች ጋር፤ የራሴው መ/ር ለዚያው ትልቅ ቦታ የሰጠሁት እንደዚህ ሆኖ ከማየት የበለጠ ለእኔ ውርደት የለም፡፡ በባዕድ ሀገር ተዋርጄ ያካበትኩትን ሀብት ሀገሬ አምጥቼ ሳፈሰው ሰው ላፈራበት በተለይም ደግሞ የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶችን ልቅርጽበት እንጂ ያለ ዕድሜያቸው ተቀጥፈው እንዲቀሩ የማደርበት እንዲሆን አስቤ አይደለም፡፡ ትላልቅ ጸሐፍትም ሲናገሩ መ/ር ሁለት አይነት ሰብዕና ሊኖረው አይገባም አንዱ በትምህርት ቤት ሌላው ደግሞ ከት/ቤት ውጭ የሚያሳየው ያሉት፤ ትክክል ነው ብዬ የማስበው በአፈወርቅ ነበር፡፡ ግና ምንያደርጋል ፤ይኸው፤ እርሱንም አምላከ ተክሃይማት እበሩ ላይ ማንነቱን አሳየኝ፡፡ እርሱስ እንደፈለገ መሆን ይችላል፤ የልጅቷ ህይወት ግን ያገባኛል፡ ያሳስበኛል፡፡ ዛሬ የዚች ታዳጊ ህይወት ሲበላሽ ወዳልሆነ አቅጣጫ ሲቀየር ዝም እያልኩ ነገ ኮሌጄ በስነምግባር ብልሹ የተሞላ ተብሎ በሚዲያ ይቀርብልኝና አንገቴን እንድደፋ ያደርገኛል፡፡ ስለዚህ ይህ ነገር ብለው ወደ አንድ ውሳኔ የደረሱ በሚመስል መንገድ መኪናቸውን በፍጥነት አቆመው ሊያነግሩት አሰቡ፡፡ ይሁን እንጅ እርሳቸው በኃሳብ ሲብሰለሰሉ አፈወርቅና ትግስትም ከአይናቸው ራቁ የመኪና ማቆሚ ቦታም ቶሎ ሳያገኙ ቀሩ፡፡ አጠገባቸው ያለቸውና በቅርቡ ከባህር ማዶ መጥታ በኬሌጃቸው ስርዓተ ጾታ ክፍል ተመድባ የምትሰራው ልጃቸው ትቅደም ዳድ ለምንድነው በሃሳብ ጭልጥ ያልከው ቶሎ ፓርክ ባለማድረግህ በርካታ ሰዎች ከኃላችን እየመጡ ጥሩ ጥሩውን ቦታ ያዙት፤ ደግሞ ገዳም መጥተን በኃሳብ ትሰምጣለህ እንዴ ካሞን ዳድ ዩ አርኖት ራይት ኦኬ. አላቻቸው በልጅነት ቁጣ፡፡ ታውሰንድ አፖሎጅ ፕሊስ፤ ሳላስበው ነው፡፡ አይ ዊልኖት ሪፒት ኢት ኤጌን ብለው የልጃቸውን ጉንጬ ነካ አድርገው ይቅርታ ጠየቁዋትና አመች ባልሆነ ቦታ መኪናቸውን አቁመው ወደ ገዳሙ ውስጠኛ የአጥር በር አቀኑ፡፡ አቶ አጽናፈ ስሜታቸው ቶሎ ቶሎ የሚለዋወጥ እና በውስጣቸው ምንም ክፍት የሌለበት ትልቅ ኢትዮጲያዊ ስብዕና የተላበሱ ሰው ናቸው፡፡ ለ 21 ዓመት የኖሩባትን ሀገረ አሜሪካን ትተው ሚስታቸውንና እዚያው ለመኖሩ የፈለጉ ሁለት ልጆቻቸውን ትተው ሶስት ፈቃደኛ ልጆቻቸውይዘው ኢትዮጲያ ሀገራቸው ከመጡና ባልተነካው የቱሪዝምና ሆቴሎች ዘርፍ ተሰማርተው ለሀገራችን እድገት የበኩላቸውን ጥረት ማድረግ ከጀመሩ አስራ ሁለተኛ፤አመት ሆኗቸዋል፡፡በትውልድ አካባቢያቸው የከፈቱት ባለሶስት ኮኮብ ሆቴልን አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር፤ዘወትር ሄደው አያዩትም፡፡ ልባቸው በሙሉ ያለው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በከፈቱት ኮሌጃቸው ላይ ሲሆን ምሩቃኖቻቸው የት እንደገቡ ምን ያክል ውጤታማ እንደሆኑ ዘወትር አጥብቀው ይከታተላሉ፡፡ በተለያዩ ጊዜያት በግል ስልካቸው በኢሜላቸው የሚመጡላቸው መልዕክቶች ከኮሌጅዎ ተመርቄ እንትን ተብሎ በሚጠራ አስጉብኝ ድርጅት ውስጥ ቱር ጋርደር ሆኛለሁ፤ አዳማ አዲስ አበባ፤አዋሳ፤ባህርዳር አዲስ በተከፈቱ፤ ባለኮኮብ ሆቴሎች ውስጥ በስራ አስኪጅነት ተመድቤ እየሰራሁ እገኛለሁ፤ ለዚህም መላ የኮሌጁን ማህበረሰብና ባለቤት የሆኑትን እርስዎን በከፍተኛ ደረጃ አመሰግናለሁ፡ የሚሉት መልዕክቶች ሲደርሷቸው፤ ውሳኔያቸው ምንያክል ትክክል እንደነበር ይገነዘባሉ፡፡ አቶ አጽናፈ ሰብለንና አፈወርቅን ደብረሊባኖስ ገዳም ባዩዋቸው ማግስት ማልደው ነበር ወደ ስራ ቦታቸው የሄዱት፤ መንገድ ላይ እያሉ የትላንቱ ነገር ትዝ አላቸውና እንደገና በሃሳብ መብሰልሰል ጀመሩ ቀስ እያሉም ውስጣቸው በንዴት መጦፍ ጀመረ፡፡ ጉዳዩን በራሳቸው ከአፈወርቅ ጋር ሊመክሩበት አሰቡና ወዲያው ሃሳቡን ውድቅ አደረጉት፡፡የዚያን ዕለት አቶ አጸናፈ አፈወርቅን ባልተለመደ ሁኔታ ፊታቸውን ከስክሰው ሰላምታ ሰጥተውት በፍጥነት እየተራመዱ አለፉት፡ አፈወርቅ አቶ አጽናፈ፤ያለውትሮዋቸው፤ቀዝ ቀዝ ያለ ሰላምታ እንዴት ሊሰጡኝ ቻሉ ብሎ ግን ብዙው ሳያሳስበው ወደ ወትሮው ስራ ቀጠለ፡፡
ዕለተ ባላንታዬን ጥር 6/2008 6፤40 መከኒሳ ቤቴ
ሰብለና አፈወርቅ ገዳም ሄደው በተመለሱ መጨረሻው ሳምንት አርብ ከሰዓት በኃላ ሰብለ አፈወርቅን ለማግኘት ወደ መምህራን ቢሮ ስታቀና አቶ አጥናፉ ከርቀት በአይነ ቁራኛ እየተከታተሉዋት እንደሆነ ማንም አያውቅም፡፡ ሰብለ መ/ራኑ ማረፊያ በር ላይ ቆም ብላ አንገቱዋን ወደ ውስጥ አስገብታ የምትፈልገውን ሰው መመልከት ጀመረች፡፡ የፈለገችው ሰው አለ ግን ከማዶ
የጥግ ላይ ኮምፒዩተሩ ላይ ስላቀረቀረ በፍጹም አያያትም፤ ዘው ብላ እንዳትገባ በርካታ መ/ራን ስላሉ ዕፍረት ተሰማት፡፡ ሰብለ እንደዚህ ዘመን ተማሪ ብዙ ደፋር አይደለችም፤ በተለይም በኮሌጅ ቅጥር ግቢውስጥ እያለች፤ ረጋ ትላለች፡፡ ይህ ባህሪዋ በርካታ መ/ራኖቿ፤የተለየ አመለካካት እንዲኖራቸው አድርጓታል፡፡ ግራ ገብቷት ቆማ ልሂድ ወይስ ልግባ እያለች ስታመነታ ዞር ስትል አቶ አጥናፍ ወደ እርሷ እየመጡ መሆኑን ተመለከተች፡፡ በመሆኑም እርሳቸው ወደ ውስጥ የሚገቡ ከሆነ እንዲጠሩላት አስባ ጠበቀቻቸው፤ ወደ አጠገቡዋ እየቀረቡ ሲመጡ ግን እይታቸው ጥሩ አለመሆኑን ስትረዳ፤ዝም ልታላቸው ፈለገች፡፡ እርሳቸውም አጠገቧ ከመድረሳቸው፤በቁጣ መንፈስ ምን እየሰራሽ ነው፤ይህ እኮ የመምህራን ማረፊያ ነው፤የምትፈልጊው መ/ራን ካለ ክፍልሽ ውስጥ ሲመጣ ጠብቀሽ አግኝው፤ ከዚያ ውጭ ግን በትምህርት ሰዓት በዚህ አካባቢ መምጣት መ/ራን መረበሽ ጊዜን አላገባብ መጠቀም ስለሚያመጣ አሁን ከዚህ ቦታ ዞር በይ እባክሽ አሉዋት፡፡ ከንግግራቸው ጠንካራነት ባለፈ የፊታቸው ገጽታ በጣም ያስፈራ ስለነበር ሰብለ ወዲያውኑ ከአካባቢው ተሰወረች፡፡ እንደዚህ ዓይነት ገጠመኝ ገጥሟትም ስማያውቅ በጣም፤ግራ ተጋባች፡፡ አፈወርቅን በዚህ ሰዓት ደግሞ ካላገኘችው በሚቀጥሉት ቀናትም ላታገኘው ትችላለች፡፡ እጅግ በሚገርም ሁኔታ እርሱም ስልኳን እርሷም ስልኩን ስላልተለዋወጡ በስልክ እንኳ መገናኘት አይችሉም፡፡ ሰብለ በጣም ተናደደች ሳላገኘው፡ሀሉት ቀን ሙሉ ልንለያይ ነው፡፡ ወይ አምላኬ ምን እየሆንኩ ነው ግን አለችና ፈገግ፤አለች፡፡ እነሰብለ በመጨረሻውን ክፍለ ጊዜ ኮርስ የሚሰጣቸው መ/ር በጣም ስለዘገዬ፤ በሩ ላይ ቆመው እንሂድ አንሂድ እየተባባሉ ባለበት ሰዓት፤መ/ር አፈወርቅ ከመ/ራን ማረፊያ ቦርሳውን አንግቦ ቁልቁል በደረጃው ሲወርድ ሰብለ ከርቀት ስላየችው፤ ጉዞዋን ወደ እርሱ አደረገች፡፡ ጓደኛዋ ሀረግ ሰብሊ የትነው ስትላት ቆይ መጣሁ ቲቸር አፈወርቅን፤ ማግኘት እፈልጋለሁ፤ መጣሁ ብላት ፈጠን እያለች ስትራመድ፡፤ በርከት ያሉ የክፍሏ፤ ተማሪዎች ከትምህርት ጋር ለተያያዘ ጉዳይ እንጂ በሌላ ጉዳይ እንዳልሆነ አልጠረጠሩም፡፡ አፈወርቅ ግቢውን ሊወጣ ሲል ሰብለ ጥበቃውን በምልክት እንዲያስቆመው ነገረችው፡፡ ጥበቃውም አፈወርቅን ሲያስቆመው አፈወርቅ መለስ ሲል ሰብለ ጂን ስ ሱሪ ለብሳ ወደ እርሱ እየመጣች መሆኑን ሲመለከት እርሱም ወደኋላው መራመድ ጀመረ፡፡ ልክ እንደተገናኙ ብትስመው ፍላጎቷ ቢሆንም ፈራ ስለምትል እጇን በትህትና ለሰላምታ ዘረጋችለች፡፡ ሰብለ እንዴት ነሽ፤ ትምህርት እንዴት ነው ፤ደግሞ ይህንን ሱሪ መልበስ አታቆሚም፡ አይደለም እኮ ቲቸር ነግሬህ የለም እንዴ ይህችን ሱሪዬን በጣም ስለምወዳት እስከምታልቅ ድረስ ነው፤ደግሞ በደንብ ሳልማር ሱሪ መልበስ መተው አይከብደኝም፡ አለችውም በአስተምረኝ ፍላጎት፡፡ እምነት በመማርና በእውቀት ብዛት ሳይሆን በማመን ነው፤እሺ፤ ደግሞ አንች ለመማር ፈቃደኛ ሁኝ እንጂ የሚያስተምር ሞልቶ የለም እንዴ ሲላት ቲቸር እኔ እኮ የሆቴል ኦር የቱሪዝም ኮርስ አይደለም የምልህ አለች ቀልድ ለመፍጠር እየመከረች፡፡ አረ ፈለጣ፤ አንች ቆይ እሺ ከግቢ ውጭ ላግኝሽ ሲላት ፍላጎቱዋ ስለሆነ እኔም እኮ ለእርሱ ነው የመጣሁት ነገ እኛ ቤት ለምን አትመጣም፤ ስትለው አይመስለኝም ነገ አንድ ጉዳይ አለኝ፤ በስንት ሰዓት ተጀምሮ በስንት ሰዓት እንደሚያልቅ አላውቅም፤ ግን ስልክሽን ስጭኛና ልደውልልሸ ሲላት ቁጥሩን ብቻ ሳይሆን ፈቃደኛ ከሆንክ አፓራተሱንም ውሰድ ቲቸር አለችው፡፡ ዛሬ አፍ ለቆብሻል ምንድነው ነገሩ፤ አርብ ስለሆነ ነው አይደል፤ ከትምህርት ልትገላገይ ስለሆነ ነው ፡፡ ኖኖ አይደለም በቃ አለ አይደል፤ ዝም ብዬ ፡፡ ለአንተ ስልኬን ቆርቶ…. ራሴንም ብሰጥህ ልትለው አሰበችና ዝም አለች፡፡ በቃ እደውላለሁ፤ አይ አንተ እንዳትረሳው አሁኑኑ ፔጅ አድርግልኝ ስልክህን ልያዘው እኔ እደውላለሁ፡አለች፡፡ ዛቲ ኢዝ ጉድ እደውላለሁ አላትና ተሰነባብተው ተለያዩ፡፡ ሰብለ በደስታ እየተፍነከነች፤ ወደጓደኞችዋ ስትመለስ መ/ሩ መጥቶ ተማሪዎች ገብተዋል፡፡ ብዙ ስላልቆየች ስታንኳኳ፤እንድትገባ ተፈቅዶላት ገባች፡፡የስልኳን፤ድምጽ አጠፋችና በእጇ ይዛ ትምሀርቱን ለመከታተል ሙከራ አደረገች፡፡ ግን ወዲያው ወዲያው ስልኳን ትገረምመው ነበር፡፡ ስልኳ ግን በፍጹም ምንም ጥሪ፤ ሊቀበል አልቻለም፡፡ 15 ደቂቃ እንዳለፈ ሰብለ ተሰፋ ቆረጠች፤ለምን አይደውልም ስልክህን ብየው አልነበረም፤ ምን ሊኮራ ነው ወይስ ምንድነው፤ እያለች በልቧ ኃሳብ ታወጣለች ታወርዳለች እንጂ ትምህርቱን በፍጹም አልተከታተለችውም፡፡ አፈወርቅ ደግሞ በዚህ ሰዓት ትምሀርት ላይ ስለምትሆን መደወል ተገቢ አይደለም ብሎ ስላመነ፤ ሊደውላላት አልፈቀደም፡፡ ሰብለ ከኮሌጅ ጓደኞቿ ፤ረዘም የሚለውን የአርብ ዕለት የመጨረሻ ጨዋታና ሰላምታ ከተሰጣጡ በኋላ ወደ ቤቷ ልታቀና ታክሲ ሰልፍ እንደያዘች በጅንስ ሱሪያዋ ውስጥ ያለው ሞባይልዋ፤ ተንፈራፈረ፤ደንግጣ ቶሎ አውጥታ ስታየው አሁን የተለየችያት ሀረግ ናት፤ ብሽቅ ብላ አቤት እህቴ ምንሆንሽብኝ፤ አይ የሆነ ነገር ሳልነገግርሽ ብዬ ነው ስትላት የሚነገራትን ሚስጢር ለመስማት ከሰልፉ ወጣ ስትል፤ አደራሽን ዳር ዳሩን እንዲሁም መንገድ ስታቋርጭ በተሰመረበት ላይ እሺ ብላ ረጂም ሳቅዋን ለቀቀችው፡፡ ሰብለም አፈር ብይ ብላ ስልኳን ዘጋችውና ወደሰልፏ ገባች፤ ወዲያውኑ ታክሲው መጣና መጨረሻ ወንበር ላይ አንድ መልከመልካም ወንድ አጠገብ ተቀመጠች፡፡ ወጣቱ፤ሰብለን ለመላከፍ እያሰበ እያለ፤ስልኩ፤ጮኸና ረዳቱን ይቅርታ ጠይቆ ወረደ፡፡ በምትኩ አንድ እናት ሰብለ አጠገብ ተቀመጡ፡፡ ሰብለ፤ረጅም የምትለውን የታክሲ ጉዞ፤ ጀምራ ትንሽ እንደተጓዘች ስልኳ ጮኸ፤ አውጥታ ስታየው የማታውቀው ቁጥር ነው፤ አፈወርቅ ይሆናል ብላ አሰበችና ላንሳው አላንሳው እያለች ስታመነታ ጥሪው ተቋረጠ፡፡ በጣም ደነገጠች፤አውጥታ አየችው፤ቁጥሩን አታውቀውም፤ልትደውል አሰበችና ደግሞ ፈራች፤ትንሽ ቆየችና መደውል ጀመረች፤ ነገርግን ኔት ወርኩ በፍጹም ሊያስደውላት አልቻለም፡፡ አንዴ ጥሪው ይወድቃል አንዴ የደውሉላቸው ደንበኛ… ይላል፤ ሰብለ ቴሌን በስድብ ወደረችበት፡፡ የቴሌከሙኒክሽን ሠራተኛ አጠገቧ ቢኖር እርግጠኛ ነኝ መጣላቱ አይቀርም፡፡ አፈወርቅም ለሰብለ ደጋግሞ ቢሞክርም በፍጹም ማግኘት አልቻለም፡፡ በቃ በዚች ሀገር ስልክ ለሸክም ብቻ ነው የተፈጠረው፤ ለምንፈልገው ሰው በምንፈልግት ሰዓት መደወል፤ጥሪ መቀበል ካቻልን የሞባይል መያዝ ጥቅሙ ምንድነው፡፡ እንዴት ሞባይል አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጀምሮ ላለፍት አስር ዓመታት ይህ ችግር አይፈታም፡ የሚገርም ነው፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ፤ አመራርና አስተዳደር መስሪያቤቱ እንደተዳደር ሙከራ ተደረገ ለውጡ ግን ምንም ሊታይ አልቻለኝም አለ፡፡ አቶ አጥናፉ በሚያከብሩት አፈወርቅና በዚች ልጅ መካከል ያለው ግንኙነት ረፍት ነስቷቸዋል፡፡ የውጭውን አለም ቀምሰው ስለተመለሱና ሀገሪቱ ላይ ያለውን የትምህርት ስርዓት በደንብ ስላላወቁት እንጂ ለተማሪው ማርክ በገንዘብ እንዲሁም በጾታዊ ግንኙት የሚጨምር ፍላጎቱንም አላሟላ ካለች ውጤቷን እስከመቀነስ ከምትማርበት ት/ቤት እንድትባር እስከማድረስ የሚደርስ ከመደበኛ ት/ቤት እስከ ዩነቨርስቲ ድረስ በርካታ መ/ር እንዳለ ማን በነገራቸው፡፡ ምግባረ ብልሹነት የስርዓቱ መገለጫ እስኪመሰል ድረስ ባለፉት አመታት ከመንግስትም ሆነ ከግል የትምህርት ተቋማት በርካታ ወገኞች በተለይም ሴቶች በፍላጎታቸውም ሆነ ያለፍላጎታቸው፤ለትምህርት ስርዓቱ መበላሸት ለመምህራኖቻቸው ትልቁን በትር አቀብለዋል ማለት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ በቁጥር ጥቂት ቢሆኑም የአንዳድ መ/ራን አላስፈላጊ የሆነ ፍላጎት ታጋፍጠው ወደ ሚፈለገው ቦታ ድረስ በማድረስም አንገት ለአንገት ተናንቀው ውጤታማ የሆኑ ጠንካራ እህቶችን ማየት ችለናል፡፡ ቁጥራቸው አነስተኛ ስለሆነና ይህም ድልና ዝናቸው ደምቆ ስለማይወጣ የምንሰማው ደካማ የሆነቸውን ሴትና በደል ደርሶባት እየተንገላታች፤ያለቸውን እህት ታሪክ ነው፡፡ አቶ አጥናፉ አንዳዴ ከስሜታቸው ወጣ ሲሉ ይህ ልጅ ወጣት፤ነው ዕድሜውም ፈተና ሊሆንበት ይችላል፤ ለምን አቅርቤ አላወያየውም ብለው ያስቡና ደግሞ እንደገና ለምን የሚለው ውስጣዊ ንዴታቸው እንደገና ገንፍሎ ይነሳል፡፡ አቶ አጥናፉ ዘወትር፤ቅዳሜ ከሰኣት ከልጃች ጋር፤ራሳቸው ፕሮግራም አላቸው፤ አንዳንዴ አብረው ወክ ያደርጋሉ አንዳንደ ከከተማ ወጣ ብለው ያመሹና ይመለሳሉ ሌላ ጊዜ ቤታቸው ቁጭ ብለው ቡናቸውን እየጠጡ ይጫወታሉ፡፡ በዚህ ሳምንት ደግሞ በልጃቸው ወደፊት የትዳር አጋር ዙሪያ ለመምከር እንጦጦ ተራራው ላይ ወጥተው ለመጫወት ቀጠሮ ይዘዋል፡፡ ትቅደምዬ እባክሽ ጓደኛ ያዥና ትዳር መስርች፤ የልጅ ልጅም አሳይኝ፡ የሚለው የዘወትር ጥያቄያቸው ነው፡፡ በርግጥ በዕድሜ ደረጃ ትቅደም ገና 24ኛ አመቷ ነው፡፡ ለማግባትም ዘገዬች የምትባልበት ዕድሜ ላይም አይደለችም፡፡ አብዛኛውን ጊዜዋን ውጭ ስላሳለፈች ሀገርቤት ከመጣችም ዘወትር ከአባቷ አጠገብ ስለማትለይ ፈላጊ እንኳ ቢኖራትም አጋጣሚ አመች ስላሆነ የወንድ ጓደኛ የላትም፡፡ ትቅደም ደግሞ እስከአሁን ካየቻቸው ወንዶች ስሙና ማንነቱን የማታውቀው በአባቱዋ፤ኮሌጅ ውስጥ የሚያስተምር አንድ ሰው አይታለች፡፡ ምኑን እንደወደደችው ለእርሷም ግልጽ ባይሆንም በአንድ ወቅት እርሷ ከአባቱዋ ጋር መኪናዋን አስነስታ ስትወጣ በመኪናዋ ስፔኪዮ፤አይታዋለች፡፡ ነጭ ሸሚዝና ለብሶ ጥቁር መነጽሩን ሰክቶ ከኃላ ሲመጣ፡፡ አባቱዋ ባይኖሩ ኖሮ የዚያን ዕለት ጠብቃ በደንብ ትመለከተው ነበር፡፡ ግን አባቱዋ ትቅደም እባክሽ ቶሎ መድረስ ስላለብን ነጂው ወይም እኔ ልያዘው ስላሏት አባትዋን አክብራ ቶሎ መኪናውን ነዳችው እንጅ፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ብዙ ጊዜ ባለቻት ትርፍ ሰዓት ግቢ ውስጥ ተንቀሳቅሳለች አንድ ጊዜ ብቻ ክፍል ውሰጥ ሊገባ ሲል ተመለከተችው እንጅ በፍጹም አይታው አታውቅም፡፡