እንደአለመታደል ሆኖ ወይንም ለበርካታ አመታት፡ በአማራ ላይ በተሰራ የውሸት ድራማ ፡ የአማራ ህዝብ፡ ክልል ተብሎ ከተከለለ ወዲህ፡ ሰላም አግኝቶ የሚውልበት ቀናት በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ ምንም፡ እንኳ ለተወሰኑ አመታት ዕረፍት ላይ የነበረ ቢመስለንም ፡ አሁን አሁን፤ለህዝብ ጆሮ ፤የሚደርሱ እውነታዎች ሲገኙ ክልሉ አንድም ጊዜ እረፍት አልባ እንደነበር ማረጋገጫዎች ናቸው፡፡ ለእረፍት አልባነቱ በርካታ አካላት ድርሻ ቢኖራቸውም፤
v የህዝቡን ስነልቦና የተረዳ መሪ አለመኖር፡
v ሁሉም ያልፋል፡ሀገር ትቀድማለች እያለ ከቤቱ አስበልጦ ለሚወዳት፤ ሀገሩ ቅድሚያ የሚሰጥ ህዝብ መብዛቱ፡
v አንዳንዱም፡
የሚወራው ና ልብወለዳዊ ዜናው፡ እውነት የመሰለው መኖሩ፤
v ክልሉ አንድ እንዲሆን የሚሰራ አካል አለመኖሩ፡፡
v አሁን
አሁንማ በተገኘችው ትንሽ የተስፋ ጭላጭል የሚፎክር፤የሚጨፍር አካል መብዛቱ፡ የተገኘውን ድልና የታሪክ አጋጣሚ፡ ጠብቆ ለበለጠ ድልና
ታሪክ ለመነሳሳት፤ የሚሰራ አካል መጥፋቱ፡ሞዴል የሚሆን፡ ገበሬው
ድረስ ወርዶ የሚመለከት አመራር፡ መጥፋቱ፡ ክልሉ ካሉት ወረዳዎችና ዞኖች ይልቅ የአፍሪካ መዲናን ለመጉብኘት፡ ናፋቂ መብዛቱ፡
v ችግሮችን በቅደም ተከተል ለመፍተታ፡ ቅንጅታዊ አሰራር መጥፋቱ፡ ባለስልጣኑም፡ ወጣቱም፤ባለሀብቱም
ሁሉም እኔ ብቻ ትክክልነኝ ማይ መብዛቱ የአንበሳውን ድርሻ ይስዳሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ (በ
1980ወቹ አጋማሽ ላይ ፕሮፈሰር አስራት ወልደስ፤ ስለ ሸዋ አማራ ብቻ የሚታገሉ የሚመስለው በርካታ የጎጃምና የአማራ ሰው እንደነበር እንዲሁም ስለ ፕሮፈሰሩ፡
ምንም መረጃ ያለው ሰው እንዳልነበር፡ ባህርዳር እያለሁ ከማረጋገጤ ባሻገር፡ “ለለውጡ” አስተዋጽኦ በነበረው የፋኖ እንቅስቃሴ ወቅትም
ሸዋ ዝም ያለው በ1980ዎቹ ጎንደር ዝም ስላለ ነው ብሎ አንድ ሰው አጫወቶኛል፡፡)
ባለፉት ሁለትና ሶስት አመታት ያለው መከራና ስቃይ ግን ከሁሉም የበለጠና የመረረ፡
አማራ ካልሞተናካልተፈናቀለ ሀገሪቱ ትበተናለች፡ መንግስቱም አይጸናም የተባለ ይመስል፡ አማራ ከክልሉ ውጭ ቀርቶ በራሱ በተባለው
ክልልም ጭምር መከራን እየገፋ ይገኛል፡፡ እርግጥነው፤ መንግስት መንግስትነቱ የሚረጋገጠው በስሩ ያለው ህዝብን አንድ አደርጎ፤ ያፈነገጠ
ካለ መክሮ ካልሆነም ተገቢው ቅጣት ቀጥቶ፡ ከስህተት በማረም ነው፡፡ ሰሞኑን በሚነገረው ህጋዊ በሆነ አደረጃጀትም ይሁን በሌላ ምክንያት፡
ክልሉ እንኳ መረጃ የሰጠበት ታሳሪ ቁጥር 5 ሺህ ደርሷል፡፡ 5 ሺህ ሰው ለመያዝ ስንት እንደሞተ፤ በዚህ ሰበብ ስንት እንግልትና
መከራ እንደደረሰ፤ ለጊዜው ባይታወቅም፡ ልጇ የታሰረባት እናት፤የትዳር አጋሩ የተንገላታባት ሴት ወ/ሮ ወይንም አባወራ፤ የት እንደታሰሩ
እንኳ መረጃ የሌላቸው የቤተሰብ አባላት ስቃና ጭንቀት፡ ከመርግ የከበደ እንደሆነ ሰብአዊ ፍጡር፤ሁሉ ይረዳዋል ብዬ አስባለው፡፡ ይህ አፈና፤አሁንም እንደሚቀጥል እየተነገረ
ነው፡፡ እኔ ህግ በማስከበር ረገድ ከማንም የተለየ ኃሳብ የለኝም፤ ሕግ ይከበር፡ ግን ህግ ሲከበር
የተጠረጡ አካላት በራሳቸው
ወደ ህግ እንዲመጡ ጥሪ ቢደረግላቸው፡
የተያዙ ማናቸውም አካላት ስለመያዛቸውና
ስላሉበት ሁኔታ ቶሎ መረጃ ለቤተሰብ ቢሰጥ
የጤናና መሰል ችግር ያለባቸው
ተጠርጣሪዎች፡ የባሰ ችግር ውስጥ እንዳይገቡ ጥንቃቄ ቢደረግ
ህግ የጣሰ ነው፤ የተባለን
አካል ለመያዝ በሚደረግ ሂደት ህግ አስከባሪው ህግ እንዳይጥስ ቢደረግ