ውለታ
ቢሱ ምስኪን ህዝብ
የሀገሬ
ጉዳይ በጣም ያሳስበኛል፡፡ የወገኔ እንግልት፤ ስቃይና ከሰብአዊነት፡በታች የሆነው ሞቱ ህሊናዬን ይረብሸዋል፡፡ ከሰው ጋር
ለመነጋገርና ለመወያየትም አንደበት ያጥረኛል፡፡ ይህንን ሁሉ ግፍና መከራ የሚቀምሰው ለምን እንደሆነ አልገባኝም፤ሊገባኝም
አይችልም፡፡ ሀገርናታሪክን ጠብቆ ባቆየ፤ በሄደበት ሁሉም ሀገሬነው ብሎ በኖረ፤ እምነትና ማተቡን አጥብቆና ጠብቆ በኖረ፡፡
እስከሚገባኝ ከዚህ ውጭ፤ምንም ጥፋት የለበትም፡፡ ታዲያ ለዚህ ክብርና ሽልማት ባይገባው፡የመኖር መብት፡ለምን ይነፈገዋል? ጠላት
ሲመጣ ምንሽሩን አንግቦ፤ሰላም ሲሆን በሬዎቹን ጠምዶ አርሶ፡እንደእምነቱ የሚያምነው አመሰግኖ ከእኔ ይልቅ ለልጆቼ ብሎ ራሱን
ወደ ሁዋላ በማስቀረቱ፡፡ ይህ ህዝብ፤ መንግስት ችግር፤ሲገጥመው ለሀገር ሞተህ ቅርስና ታሪክ ጠብቀህ እየተባለ በአፍ
እየተንቆለጳጳሰ፤በሽልማቱና በምስጋናው መንደር፤ ዝር እንዳይል ከመከልከል ባነስ ለምን ይገደል? ለምስ ይንገላታ? በንጹህ እምነቱ ሁሌ የሚያሰበው አምላኩ፡ አይኑን ባዞረ ጊዜ ገዳዮቹ የት እንደምትገቡ አስቡ፡፡ሀገር እመራለሁ፤ ክልል እመራለሁ ብለህ ወንበር ላይ
ያለህ ባለስልጣን፤ ወንበር ላይ ያስቀመጠህን ምስኪን ከሞት መታደግ ካልቻልክ በምን ሂሊና ነው፡፡ ህዝባችን ብለህ የምታወራው? ላንተ
የህዝብ ሞትና ስቃይ የሚገባህ፡ የስጋ ክፋይ ልጆችህ ሲሞቱ ይሆን? ከአሁኑ ጠንክረህ ካልሰራህ፤ ለእርሱም ትደርስበታለን፡፡ በንጹህ
ህዝብ ላይ የማይገባ ግፍና በደል እየፈጸመ ያለው አካል ነገ አንተን ቢምርህ፡ ከምላሴ ጸጉር ንቀል፡፡ ህዝብ ነህ የህዝብ አካል
ህዝብ ሲገደል፡ ለምን በል ጠይቅ፡ዝም ብለህ እንደወራጅ ውሃ አትውረድ፡፡
No comments:
Post a Comment