የህዳሴው ብርሃን
የህዳሴ
ግድብ መገንባት ከጀመረ፡ መጋቢት 2003 ዓ.ም ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር የነበረውን የንጉስ ኃ/ስላሴንናየቀድሞው፤የህዳሴው
ግድብ ፎቶ ግራፍ እንዲሁም አብሮ የተጻፈውን መልዕክት ሳነብ ፡ ሁሌም
ውስጤ ያዝን ነበር፡፡ በራሳችን ሀብትና ንብረት በሌላ አካል መልካም ፍቃድ ካልሆነ በስተቀር መጠቀም እንደማንችልና ንጉሱ ውስጣቸው እያረረ ለትውልድ ያስተላለፉት የቁጭት መልዕክት፡
እንዲህ ይል ነበር
እኛ አሁን ለመገንባት አቅሙ ላይኖረን ይችል ይሆናል፤ ነገር ግን
ዛሬ እኛ በምናስቀምጠው ራዕይና አቅጣጫ ነገ ከነገ ወዲያ ልጆቻችን ይገነቡታል፡፡
ንጉሰ ነገስት አጼ ኃይለ ስላሴ1957
በዚህ
ንግግር የቀድሞው ንጉሳችን ምንያክል ውስጣቸው እየደማ፤ የተናገሩት ቢሆንም በቀጣዩ ትውልድ ግን የነበራቸው ተስፋ ግን በእጅጉ ያስደስታል፡፡
የህዳሴው፡
ግድብ ንድፍ በ50 ብር ላይ ንጉሱ ከውጭ ከግድቡአማካሪዎቻቸው ጋር
1957
የቤታችን ታላቁ ልጅ እና ለእኔ ከቀለም ብርኃን፡እንድገናኝ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው ታላቅ ወንድሜ ቀለመወርቅ እጅጉ የተወለደው
ንጉሱ ይህንን የቁጭት ንግግር በተናገሩበት 1957 ወርሃ ታህሳስ በ 23ኛ ቀን ነበር፡፡ እናም ንገሱ እንዳሉት፡ ያ ቁጭት ያንገበገበው
በንግግሩ ወቅት 10 አመት የሆነው ልጃቸው አቶ መለስ ዜናዊ በቁጭት ሲኖር የነበረውን ኢትዮጲየዊ ሁሉ ወክሎ መጋቢት
24/2003 ዓ.ም በጉባ ሞቃታማ ቦታ የህዳሴውን ግድብ፡የመሰረት ድንጋዩን አስቀምጦ፡ የምንጊዜም ወዳጅና ጠላታችንን፡ እንድንለይበት
አደረገን፡፡ ነብሱን በገነት ያሳርፈው፡፡
የግድቡ መሰረት ሲጣል መጋቢት 24/2003. ግድቡን በኃላፊነት የመሩ
ያለፍት አስር አመታት፡ በህዳሴው ግድብ ጉዳይ በበርካታ ጥቁሮችና በጥቂት ነጮች ዘንድ ፤ ከፍተኛ ድጋፍ የነበረው ቢሆንም በመላው ነጭና፡ በነጭ ፈረስ በሚጋለቡ ጥቁሮችና፡ ነጭ፤አፍሪካዊያን ዘንድ በተለይም ደግሞ በግብጽ፡ ግን አለምን ያነቃነቅ፡ ተቃውሞ፡ ያስነሳብን ጉዳይ ነበር፡፡ ጎበዝ በጭንቅ ይለወዳል እንዲሉ ፡ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ወቅት በርካታ ነቀዞች ተነስተው ከሌለው፡ ሀብቱ ለግድቡ ከሚለግሰው ድሃ ገንዝብ፡ ሰርቀው ለግል ጥቅማቸው ቢያውሉም፡ ታሪካቸውን በደማቅ ቀለም መጻፍ የቻሉ፡በርካታ፡ድንቅ ዜጎችን ማፍራት የተቻለበት ወቅት ነበር፡፡ በአረቡ አለም በእነርሱ፤ሚዲያ በእነርሱው ቋንቋ፤ በእነርሱ ግብዣ፤እየታዳሙ፡ አፋቸውን ያሲያዙ በርካታ ጀግኖች ተወልደዋል፡፡ ጉልት፡ የምትሸጠው እናት፤ለከረሜላና ብስኩት መግዣ፤ሽራፊ ሳንቲም፡የተሰጣቸው ህጻናት፤ በአረብ ምድር የቤት ሠራተኛ የሆነችው እህት፤ በመላው አለም ተበትነው ያሉ ሁሉም ኢትዮጲያዊን፡ ባለሀብቱ፤ገበሬው፤ሊስትሮው፡ ሁሉም የህዳሴው ፡ግድብ፡የወለዳቸው፡ ጀግኖች ናቸው፡፡ ኢትዮጲያን በተመለከተ ሁሌም በአድልዋዊነቱ፡ የማይታማው የአለሙ መንግስታት ድርጅትና የጸጥታው ምክርቤት፡ የህዳሴውን፡ ግድብ በተመለከተ በግልጽና በዝግ በርካታ ስብሰባዎችንና ውይይቶች፤ ቢያደርግም፤ዜጎቿን በተለይም ደግሞ አምላኩዋን የተማመነችው ኢትዮጲያ ግን፡ ሁሉም ሲንጫጫ ዝም ብላ ስራዋን ስትሰራ ነበር፡፡ የሚገርመው በህዳሴው፡ ግድብ ዙሪያ ሲሰበሰቡ ቆዩት አካላት ሁሉ ምንም ስምምነት ላይ ሳይደርሱ፡ ግድቡ ግን የመጀመሪያውን ብርሃን ለተወለደበት ሀገር ሰጠ፡፡ በወርሃ የካቲት፡፡ ወርሃ፡ የካቲት ለእኛ ኢትዮጲያዊያን ድንቅ ናት፡ በነጭ አንገዛም ብለን በራፋችን ድረስ ፎክሮ የመጣውን ጣሊያን ገርፈን የጥቁሮችን ታሪክ በደማቅ የጻፍንበት፤ የ40 አመት ዝግጅት አድርጎ የመጣውን ያንኑ ወራሪ፡ ህዝብን ሰብስቦ ፡የንጉሴን ልደት አክብሩ፤ስጦታም ልስጥ ብሎ በራሳችን መናገሻ ከተማ ሲደነፍ፡ ሊዛን እንደማይችል፤ ቦንብ በማፈንዳት፤ቁጣችንን የገለጽንበት፡ በዚህም ተናዶ የመከራውን ዶፍ ቢያወርድብንም አንድ ሆነን እስከመጨረሻው የተፋለምንባት ወር ናት፡፡ የካቲት፡ ዳግማዊ ምኒሊክ፡ ከመላው ኢትዮጲያ እንዲ ለሀገሬ ብለው ከተመሙ ጀግኖች ጋር በመሆን በአድዋ ተራራ፤ ላይ ጣሊያንን ድል አድርጎ የነጻነት ብርሃን፤ የለኮሶባት፤ ስትሆን ዛሬም የእነዚያን ጀግኖች ተከታይ ትውልድ ከአስር አመታት ትጋት በሁዋለ በወርሃ የካቲት፡ የብርሃንን ፋና ለኩሰው ለሀገራቸው አበርክተዋል፡፡
ኢንጅነር ሰለሺ በቀለ
የካቲት 13/2022 ዓ.ም ለአመታት በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው አባይ ብርሃኑን ፡ ከተገጠሙት 13 ተርባይኖች መካከል አንዱና ን 375 ሜጋ ባይት ማመንጨት በሚችለው፤ተርባይን፡ እንካችሁ ብሎናል፡፡ አባይ ለዘመናት ሲበድለን፤ ሲያራቁተን፤ ቢኖርም አሁን ግን እንጀራ ሆነን ልንበላው፡ ብርሃን ሆነን ልንደምቅበት፡ ከጨለማ ልንወጣበት ወስኖ ወደ እናቱ ጉያ መፍሰስ ጀምሯል፡፡ ያች በጭስ እንባ ለዘመናት መከራ ስቃይ የነበረችውን እናት፡ አይዞሽ እያለ የብርሃን ተስፋ ይዞላት መጥቷል፡፡ አባይ ሆይ በዘመኔ አንተ ተገድበህ፡ ለሀገሬ ብርሃን ስትሰጥ በማየቴ ምንኛ እንደኮራሁና ደስ እንደተሰኘሁ ላይገባህ ይችል ይሆናል፡ ግና ወደፊት ብርሃንክን ተጠቅመው፡ ውጤታማ የሚሆነ የአብራክ ክፋይ ልጆቼን ስትመለከት ለዘመናት ምንኛ እንደበደልከኝ ይገባል ይሆናል፡፡ ቢሆንም ግን ይቅርታዬን አልፈግህም፡ የምትል እናት እንደምትገጥምህ ጠብቅ፡፡
No comments:
Post a Comment