Tuesday, July 8, 2025

 


                            አ-ፈ-ወ-ር-ቅ ( part-2)

ጥር 19/2008 ከምሰቱ 3.37

አባቴ የአስተርዮ ማርያም አንድ ቀን ሲቀራት ሱባዔውን ፈጽሞ ወጣ፤በውስጡ ይብሰለሰሉ ለነበሩ በርካታ ጥያቄዎችም ምላሽ አኝቷል፡፡ በቀጠሮው መሰረት ለየኔታም መልሱን ምን መሆን እንዳለበት ወስኖ፤ተቀምጠዋል፡፡ ይሁን እንጂ ቀጠሮው ከመድረሱ በፊት ወደ /ቤቱ አልተመለስም፡፡ ምክንያቱም ወደትምህርት ገበታው ሲሄድ የኔታን ስለሚያገኛቸውና ከቀጠሮ በፊት እንዳይጠይቁት ፈልጎ፡፡ ሰብለ አባቴ እንደነገረኝ ጥር 21 በዚያንም ዓመት የዋለችው አርብ ቀን ስለነበር የኔታ ከተማሪዎቻቸው ጋር ወንበር ዘርግተው ከሚያስተምሩበት በእግር የሁለት ሰዓት መንገድ ተጉዞ በአባ፤ጼዋ ለጸድቅ ገዳም ውስጥ ወደምትገኘው፤የማርያም ቤተክርስቲያን ለበአል እንደሚሄዱ አባቴ ስላወቀ እርሱም ቀድሞቻቸው እዚያ ለመገኘት ሀሙስ ማታ ወደዚያው አቅንቷል፡፡ ይሁን እንጂ ያለወቅቱ የመጣው ዝናብ ከጉዞዋቸው እንዳያስተጓጉላቸው የፈሩት የኔታ በተማሪዎቻቸው ታጅበው በዋዜማው፤ወደ ገዳምዋ ገና ከጠዋቱ አራት ሰዓት አቅንተዋል፡፡ አባቴ ወደ ገዳሙ እቀረበ ሲመጣ ለወትሮው ከገዳሙ ከሚሰማው የወፍ ድምጽ ገዝፎ የተለያዬ የተማሪዎች ዜማ ድምጽ የገዳሙ አጸድን ሰንጥቆ ሲመጣ መስማት ጀመረ፡፡ በሁኔታው ግራ የተጋባው አባቴ በዚህም ገዳም ወንበር ዘርግቶ የሚያስተምር መምህር መጥቶ ይሆን ወይስ የኔታ ቀድመውኝ መጥተዋል እያለ፤ በፍጥነት ወደ ገዳሙ፤ የሚወስደውን፤ የቁልቁለት መንገድ አገባዶ ለጥ ካለው ሜዳ ላይ ሲደርስ የኔታ በተማሪዎቻቸው ተከበው ሲያስቀጽሉ ሲመለከት ግራ ተጋብቶ ቀጥ ብሎ ቆመ፡፡ በዚህ ጊዜ አንድ ተማሪ ወደየኔታ ጆሮ ጠጋ ብሎ የሆነ ነገር ሹክ አላቸው፡፡ የኔታም ከተቀመጡበት ማን እንዳስነሳቸው ሳያውቁ ድንገት ተነሱና እሺ ሲሉ ሁሉም ተማሪ በአንድ ጊዜ ጸጥ አለ፡፡የታለ እስኪ ገብረ መስቀል ሂድ እስኪ አምጣው ሲባል በርካታ ተማሪዎች ወደ አባቴ ቀርበው አንዱ ትከሻዋ ላይ ሌላው እግሩ ላይ ሌላው ወገቡን እንቅ አድርው እየሳሙት፤ስላቆዩት የኔታ በሚፈልጉት ፍጥነት አባቴ ሊደርስላቸው ስላልቻለ፤ የኔታ ሲቆጡ ሁሉም ተማሪ አባቴን ለቀቀውና ወደፊት አጅበውት ሄዱ፡፡ አባቴ ስለ ቆሎ ተማሪ ትምህርት ቤት ጓደኞቹ ፍቅር አውርቶ አይጠግብም፡፡ መተዛዘናቸው፤ አንተ ትብስ አንት ትብስ መባባለቸው ለአባቴ ጥሩ የትምህርት ቤት ትዝታዎቹ ናቸው፡፡ ሰብለ ምንም አይነት የቆሎ ተማሪ ስዕል በውስጧ ስለሌለ ትንሽ ግራ የተጋባች ስለመሰለው የቆሎ ተማሪ ማለት ሰብለ ሁሌም ቆሎ እየበላ የሚማር ማለትአንደሆነ ተገምቻለሽ ብዬ አስባለሁ አላት፡፡ነው እንዴ እኔ እኮ ግራ ገብቶኝ ነው፡፡ አፈወርቅ በሳቅ ፈነዳ ምነው ያስቃል ትክክል አይደለም፤ የነገርከኝ ወይስ ምንድ ነው፤ እያለች ቅድመ ካኮረፈችበት ስሜት ወጥታ ዘና ማለት ጀመረች፡፡ አይ ሰብለ ለመሆኑ ከአዲስአበባ ውጭ የት ሄደሽ ታወቂያለሽ፡፡ ውይ ብዙ ቦታ ሄጃለሁ አንድ ጊዜ ቤት ሳላስፈቅድ ኮተቤ፤ ሌላ ገዜም እንደዚሁ እንጦጦ እንድ ጊዜ ደግሞ የትነበር የሄድነው ዱከም፡፡ አፈወርቅ በሳቅ እንባውን ጨረሰ፡፡ አንች አኔ እኮ ከከተማ ወጥተሸ የማታውቂ ትመስይኛለሽ፤ ለካ ብዙ ቦታ ሄደሻል፡፡ ግን እዚህ ሁሉ ቦታ መሄድሽን ቤተሰብ ያወቃል አላት አሁን በሳቅም እየፈነዳ፡፡አረ በናትህ እንዳይሰሙ ማንም አያወቅም፡፡ ከተሰማ ጉዴ ነው፡፡ አሁንም ልቡ ሊፈርስ ደረሰ፡፡ ለሁሉም ሰብለ የቱሪዝም ተማሪ ስለሆነሽ ኮሌጃችንም የተለያዩ የመስክ ጉብኝቶች ስለሚኖረው ያኔ ብዙ ቦታ ታያለሸ፡፡ የቆሎ ተማሪ ማለት ደግሞ ትርጉሙ የነገርኩሸ ሳይሆንም ምን እንደሆነ አባቴ የሰጠኝ ጥንታዊ የቆሎ ተማሪ የሚል መጽሐፍ አለኝ እርሱን አውስሽና ታነቢዋለሸ፡፡ መሰነባባቻ እንዲሆነን ከመጽሐፉ ከማስታውሰውና አባቴ በቃሉ ከሚለው አንድ ግጥም ልንገርሸ

የቆሎ ተማሪ ቢቀር ምናባቱ ዱላ ሲያነሱበት ይላል ባዛኝቱ፡፡

እንኳን ባዛኝቱ ይብል በስላሴ እኔ እወደዋለሁ እስኪትወጣ ነብሴ፡፡

ብሎ ለመሄድ ሲነሳ እናት ሰራተኛ አስከትለው ምግብ ይዘው ወደ ሳሎን ዘለቁ

 

ጥር 20/2008 ልክ እንደትላትናው መነን፡፡

ሰብለ በእንጥልል፤ የሰማችው የመምህሯ፤የህይወት ታሪክ ከመልካም አተራረክ ጋር ተዳምሮ ለመምህሯ፤የተለዬ አመላካከት እንዲኖራት አድርጓታል፡፡ ምንም እንኳ ዕድሜዋ በአፍላ የወጣት ዕድሜ ላይ ሆኖ፤ የበርካታ ወጣቶችን ስሜት የሚማርክ ቢሆንም እርሷግን የእኔ የምትለው የወንድ፤ ጓደኛ የላትም፡፡ የሰፈር ወጣቶች ልባቸው ቢመኟትም ከቤት አለመውጣቷ እንዲሁም የቤተሰቧ የአኗኗር ዘይቤና ከሚኖሩበት ሰፈር ጓላ ያለመሆኑ ማንም ደፍሮ የፍቅር ጥያቄ ሊያቀርብላት የሞከረ፤ የለም፡፡ እርሷም ቢሆን አስረኛ ክፍል ተማሪ ሳለች አንድ ስሙን እንኳ ከማታውቀው አንድ የትቤቷ ወጣት ጋር ድብን ያለ የአይን ፍቅር፤ይዞዋት ከነበረው ውጭ ማንንም አፍቅራ አታውቅም፡፡ ወጣት ግን በጣም ጎድቷት በራስ መተማመኗን ሁሉ በከፍተኛ ደረጃ ሸርሽሮት የነበረ ከመሆኑም ባሻገር በወቅቱ ሁኔታዋ ለቤተሰቡም ግራ መጋባት መንስኤ ሆኖ ነበር፡፡ ሰብለ አፈወርቅን ከመምህርነቱ በሻገር ለፍቅርም አሰበችውና እንደገና ድንጋጤ ያዛት፡፡ ይህንን የመሰለ መልክና መልካም ስብዕና ይዞ በዚያም ላይ የኮሌጅ / ሆኖ አስከአሁን ባያገባ እንኳ የእኔ የሚላት ጓደኛ ልትኖረው እንደምትችል ስለገመተች፤ በፍጹም ይህንን ላስበው አይገባም፡፡ ይልቅስ መልካም ጓደኛ ሆኖ መካሪ ወንድሜ ሊሆን ይችላል፡ ብላ ልቧ ሌላ እንዳያስብ ለማድረግ ሞከረች፡፡ ግን ደግሞ እኮ እርሱም አስተያየቱ የሆነ ነገር እንዳሰበ ያስታወቅ ነበር፡፡ መቼም ይህንን መልካምነት ይዞ ለጊዜያዊ ስሜት እንደማይቀርበኝ አስባለሁ፤ ብላ በኃሳብ መብሰልሰል ጀመረች፡፡ ቆይ ግን እኔ የእርሱ እንዳልሆን ምን ያንሰኛል እያለች ራሷን ለማየት ወደ ወላጆቿ መኝታ ክፍል ገባችን በትልቁ ቁም ሳጥን ላይ ባለው መስታወት ላይ ራሷን ማየት ጀመረች፡፡ ሰብለ ከላይ ጣል ያደረገቻትን ቦዲ ዝቅ አደረገቻትና አንገቷን ወደ ተለያዬ አቅጣጫ እያደረገች ራሷን ተመልክታ፤ አንዲት ወጣት ሊኖራት የሚችል ውበት እንዳላት አረጋገጠች፤ በዚያም ላይ በጉንጮቿ፤ላይ ያለት ስርጉዶች ለእርሷ የልዩ፤ውበት መድመቂያ የተፈጠሩ እንደሆኑ አሰበች፡፡ ሁሉም የሚመካበትን ሐር የመሰለ ጸጉሯን ብትን ስታደርገው፤ ቁንጅናዋ የበለጠ ታዬ፡፡ ታዲያ አፈወርቅ ይህንን ውበት አግኝቶ ነው እንዴውም እበዛበታለሁ፡ እሺ አልለውም እያለች ብቻዋን ፈገግ አለች፡፡ ግን ደግሞ ወዲያውኑ እርሱም እኮ ከባህሪው፤ከትምህርት ደረጃው ጋር ተደምሮ ያለው ወንዳወንድነት ማንም ቆንጆ የምትባል፤ ሴት አይኗን ሳታሽ ልታገባው እንደምትችል መገመት ጀመረች፡፡ ታዲያ ከእነዚህ ሁሉ እኔ በምን በልጬ ነው የእኔ ላደርገውም የምችለው፤ እያለች ሊኖራት የሚገባዋን የተለየ ሰብዕና ማሰብ ጀመረች፡፡ ግን አፈወርቅ እኔ ላናግረው በጣም ስጨነቅ፤ በግል ህይወት ዙሪያ ለመወያየት፤ ቤቴ ስጋብዘው ምንም ሳያንገራግር ፈቃደኛ እንዴት ሊሆን ቻለ፤ በርግጥ ያኔ ያለኝ ቤትሽ መሆኑ ደስ ይለኛል፡ ምክንያቱም እኔ ቤት ወይንም መናፈሻ ብንቀጣጠር ሊመለከትን የሚችለው የሚያውቀን ሰው ሁሉ ሊገምት የሚችለው ሌላ ነው፡፡ አየሽ /ርነት የተከበረ ሙያ ነው እኔ ደግሞ በተከበረ ሙያው , አንድ ነገር ብጨምር ደስ ይለኛል እንጅ ሙያውን ለማሳደብ እኔን ግን ሊያስደስት ከሚችል ማንኛውም ድርጊት ልታቀብ እንደሚገባኝ የአባቴ ቃል አለብኝ፡ነበር ያለው፡፡ በጣም ብልህና አርቆ አስተዋይነት ነው፡፡ ስንቱ ከአንድ በላይ ከሆኑ ተማረዎቹ ጋር እየቀበጠ የከበረውን ሙያ እንዳላሰደበው ሀሉ / አፈወቅርን የመሳሰሉ በቁጥርም ቢያንሱ አልፎ አልፎ የከበሩ ሰዎች አይታጡም፡፡ እድሜ ለእነዚህ መብራቶች፤ ሙያውን ፈጽመን እንዳንጠላው ስላደረጉን፡፡ አፈወርቅ ከነሰብለ ቤት ከወጣ በኋላ አንዲት ቀጭን ሰው የማይበዛት መንገድ ይዞ መሬት መሬቱን እያየ መንገዱን ቀስ እያለ ተያይዞታል፡፡ መሬት መሬት እየተመለከተ፤ በውስጡ እያሰበ ያለው ስለሰብለ ነው፡፡ ይህችን ልጅ ማየት ከጀመርኩ ጀምሮ ልቤ በጣም ይደነግጣል፡፡ ብዙ ጊዜ ወደ ውስጤ እንዳትገባ ጣርኩ ግን ሊሆን አልቻለም፡፡ ሁኔታዎች ከሚያለያዩን ይልቅ ማቀራረባቸውን ቀጥለዋል፡፡ እርሷ የምትማርበትን ሴክሽን ሁለተኛ ኮርስ እንዲየስተምር ተደረግሁ፤ ከዚያ ይባስብ ብሎ በምትጠይቀኝ ጥያቄዎች የተነሳና በምሰጣቸው የተለያዩ አሳይመንቶች በምትሰጣቸው ሰፋ ያሉና ከሌሎች በተለየ መልክ የምታቀርባቸው ትንታኔዎች ዛሬ እቤቷ ድረስ እንድመጣና ለጊዜው ከእናቷ ጋር እንድተዋወቅ አደረገኝ፡፡ ነገስ ምን ሊሆን ነው፡፡ ውስጤስ ምን እየተሰማው ነው፡፡ ከእርሱ ጋር ሳወራ የሚሰማኝ ስሜት በጣም የተለየ ነው፡፡ ወደድኳት ይመስለኛል፡፡ አስከአሁን በልቤ ሳስባቸው ከነበሩት ጥቂት ሴቶች መካከል የምፈልጋቸውን የያዘች ሰብለ ብቻ ነች፡፡ ስጋዊ ውበቷ ሳይሆን ውስጣዊ ስብዕናዋ ተንከባክበው ቢያሳድጉት የበለጠ ሊጎመራና ሊፈካ የሚችል ነው፡፡ ስለዚህ አምላኬ የግራ ጉኔን በዚህ መልኩ ልትሰጠኝ አስበህ ይሆን፡ አንተ ለእኔ የሚሆነው ስለምታወቅ፤ ህይወትዋ ህይወቴን ህይወቴ ደግሞ ህይወቷን የሚያስደሱት ከሆነ የአንተ ፈቃድ እንደሆን ፈቃዴን ሰጥቸሃለሁ፡፡ ይሁን እንጂ በውስጤ ያለው ስጋዊ ፍላጎት ከሆነ ከውስጤ በኖ እንዲጠፋ ታደርገው ዘንድ እለምንሃለሁ፡ አለና ካቀረቀረበት ቀና ብሎ የሚወዳትን መዝሙር በውስጡ እያንጎራጎረ መንገዱን ተያያዘው፡፡ በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ አፈወርቅ እነ ሰብለ ክፍል ሲገባ ሰብለ ቀና ብሎ ለማየት ፍርሃት እየያዛት ቢሆንም ቀስ በቀስ ግን እንደወትሮዋ መሆን ጀመረች፡፡ አፈወርቅ ግን ከወትሮውም ምንም የተለየ ሁኔታ ሳያሳይ የእለቱን ትምህርት በሚገባ አጠናቅቆ ከመውጣቱ በፊት አንድ ሁለት ተማሪዎች ጥያቄዎችን ጠየቁት፡፡ ጥያቄውን ከመመለሱ በፊት ከአሁን በፊት እንደሚያደርገው ዕድሉን ለተማሪዎቹ ሰጠ፡፡ ሰብለን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ተማረዎች በጥያቄዎቹ ላይ ያላቸውን ሃሳብ አቀረቡ፡፡ በሚገርም ሁኔታ ከመላሾቹ በሚገባ የመለሰችው ሰብለ ነበረች፡፡ አፈወርቅ፤ ሁሉንም ተማሪዎች አመስግኖ እርሱ የማጠቃለያ መልስ ሰጠና የዕለቱን ክፍለ ጊዜ አጠናቆ ወጣ፡፡ የሰብለ ሁኔታ አሁንም በውስጡ ሌላ አግራሞት ጨምሮበታል……

 

 

No comments:

Post a Comment

                             ገበር አምባ                    ስራ ፈቶ ሲያሽ ያንች ተመልካች                       በውበት ቁንጅና ማን ነበር እንዳንች፡፡          ...