Thursday, January 25, 2024

የምስራቂቷ ጎረቤታችን

 



የምስራቂቷ ጎረቤታችን ለበርካታ ዘመናት በአልሸባብ ስቃዩዋን ስታይ፤ አሽቃቧጯ፡ አሜሪካም ጭምር ሶማሊያን ለመገዝ ብላ ወታደሮችዋ አስከሬን መሬት ለመሬት እስኪጎተት ድረስ ሙከራ ያደረገች ቢሆንም፡ ሽብሩ ከሶማሊያ አልፎ ለ|ዓለም ስጋት ሲሆን ቅሌን ጨርቄን ሳትል ሶማሊያን ትታ ፤ስትፈረጥጥ፤ አልሸባብን ሰጥ ያደረገችው ሀገሬ ኢትዮጲያ ነበረች፡፡ ለዚህ አበርክቶዋ፤ ምናልባት ፡አሜሪካ አርባምንጭ አስቀምጣው ከነበረ ቁሳቁሷ የተወሰነ አበርክቶ አድርጋ ካልሆነ በሰተቀር ላደረግነው አበርክቶ፡ ዘላቂ ወዳጅነት ሳይሆን፡ ዘመን ጠብቆ የሚከዳ አስመሳይ አጋር ነው የሆነችብን፡፡

ከአሜሪካ የከፋው፡ ደግሞ፡ ኢትዮጲያን ለማጥፋት፡ እንደ አቶ ጌታቸው ረዳ ሲኦልም ድረስ አወርዳለሁ፡ የምትል የሚመስለው፡ ምስር  ( ግብጽ) ግን ሶማሊያ በአልሸባብ፡ እግር ተወርች ተይዛ የቁም ስዕሏን ስታይ፡ ስለሶማሊ በምስራቅ አፍሪካ ስለመኖርዋ፡ እንኳ መረጃ ያላት አይመስለኝም ነበር፡፡ ግን ኢትዮጲያ የባህር በር ለማግኘት በምታደርገው ጥረት ውስጥ የግብጽ መሪ እንዲህ ብለው ነበር፡፡

"የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር የሁለቶሽ ምክክር ካደረጉ በኃላ በጋራ ሆነው መግለጫ ሰጥተው ነበር።በዚህም ወቅት የግብፁ መሪ ፤ " የአረብ ሊግ ቻርተር በሉዓላዊነታቸው እና በግዛታቸው ላይ ጥቃት የሚደርስባቸውን የአረብ ሀገራት እንድንከላከል ያስገድደናል " ሲሉ ተደምጠዋል። " ግብፅ በሶማሊያ ደህንነት ላይ ምንም አይነት ስጋት እንዲፈጠር አትፈቅድም " ሲሉ የተናገሩት አልሲሲ ፤ " የግብፅ ሃያልነት ወንድማማች የሆነ ሀገሮች ላይ ስጋት በመፍጠር መሞከር የለበትም ፤ አትፈታተኑን " ብለዋል። " ግብፅን አትሞክሩ ፤ የግብፅ ወንድሞች የሆኑ ሀገራት ላይም ስጋት ለመሆን አትሞክሩ " ሲሉ የተደመጡ ሲሆን ጥያቄ ከቀረበልን ጣልቃ እንገባለን ሲሉ ተናግረዋል። የግብፁ ፕሬዜዳንት ፤ " በተለይ ወንድማማች ሀገሮች ከጎናቸው እንድንቆም በሚጠይቁን ጊዜ ለመቆም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን " ግብፅ በአንዱ አረብ አገር ላይ ጥቃት ቢሰነዘርበት ለመደገፍ ዝግጁ ነች " ሲሉ ተደምጠዋል።

ፕሬዝዳንት በንግግራቸው #የኢትዮጵያንም 🇪🇹 ስምን አንስተው ሲናገሩ ነበር።  አልሲሲ ፤ " ለኢትዮጵያ ያለኝ መልዕክት የሶማሊያን አንድን መሬት ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት አይሳካም በዚህ የሚስማማም የለም " ብለዋል።የሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነት በግብፅም በሶማሊያም ዘንድ ተቀባይነት የለውም ፤ ጣልቃ እንድንገባ ከተጠየቅን ደግሞ በሶማሊያ ላይ የሚፈጸም የሉዓላዊነት እና ግዛት አንድነት ጥቃትን ለመመከት ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል።

 

ዛሬ ያነበብኩት አንድ መረጃ ደግሞ ሶማሊያ ከአልሸባብ ጋር እየተዋጋች እንደሆነ፡ የሚገልጽ ነው፡፡ እና ለዚያች፡ በርቀት በመሆኑዋ፡ ዜናውን ላልሰማችው ሀገር ግብጽ( ምስር) ይህንን መልዕክት ማን ያድርስልን፡ ማን ይሆን ዛሬ ጉልበተኛ ነኝ እላካለሁ የሚለኝ፡ ኤርትራ ወይስ ማጣፊያው ያጠራት ሱዳን፡ እስኪ የሚላክ አካል ፈልጉ፡ አልሲስ ከቀናት በፊት በሶማሊያ ደህንነት ላይ ምንም አይነት ስጋት እንዲፈጠር አትፈለግም ብለው ነበር፡፡ እባካችሁ እንደዚያ ያሽቃበጡላት ሶማሊያ ችግር ውስጥ ነች በሉዋት፤ አደራ አደራ

No comments:

Post a Comment

                             ገበር አምባ                    ስራ ፈቶ ሲያሽ ያንች ተመልካች                       በውበት ቁንጅና ማን ነበር እንዳንች፡፡          ...